Kassaye Arage

የጨዋታ እንቅስቃሴን የማንበብ ብቃት

እግርኳሳዊ ብልሀት በእእምሮና በእግር ግንኙነቶች ላይ የተመሰረተ ነው። ይሄ ያላቸው እግርኳስ ተጨዋቾች ሜዳ ላይ አንድን እርምጃ ከመውሰዳቸው በፊት ጊዜን፣ ቦታን፣ ጥንካሬን፣ ድክመትን እና አጠቃላይ የጨዋታ እንቅስቃሴን ከሌሎች ፈጥነው የማስላት ብቃት አላቸው። የኢትዮጵያ እግርኳስ ተጨዋቾች የሚያንሳቸው ነገር ቁመት፣ ጉልበትና የኳስ ችሎታ ሳይሆን ያላቸውን ነገር እንዴት መጠቀም እንዳለባቸውና ኳስ ተጋጣሚያቸው እግር ውስጥ ስትገባ ምን ማድረግ እንዳለባቸው አለማወቃቸው […]

Continue reading
Bildnummer: 01032249  Datum: 03.09.1994  Copyright: imago/Sven Simon
Matthias Sammer (BVB) gibt lautstark Anweisungen; quer, close, Gestik, zeigen, Fingerzeig, Anweisung, Schrei, schreien Saison 1994/1995, Frankfurt - Borussia Dortmund 4:1, Vdia Frankfurt / M. Fußball 1. BL Herren Mannschaft Deutschland Einzelbild pessimistisch Aktion Personen

ወርቃማው ጀርመናዊ ኮከብ

ጀርመን ለአለም እግርኳስ ካበረከተቻቸው ታላላቅ ተጨዋቾች መካከል አንዱ ማቲያስ ሳመር ነው። ሳመር በተለይ እ.አ.አ በ1990 ዎቹ አጋማሽ በእግርኳሱ አለም የነገሰበት ወቅት ሲሆን ከሀገሩ ልጅ ፍራንዝ ቤከንባወር በኋላ አንድ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ከመሀል እና አጥቂ ስፍራ ተጨዋቾች የበለጠ ጎልቶ እንዲጠራ በማስቻል ስሙ ዛሬም ድረስ የገነነ ድንቅ የእግርኳስ ሰው ነው። ይህ አጭር ዝግጅት ከማቲያስ ሳመር ጋር አድማጮችን […]

Continue reading
Sepp and JH

ፊፋ እና ፖለቲካ

ሴፕ ብላተር፣ አጋሮቻቸው እና ደጋፊዎቻቸው በተለይ ባለፈው ግንቦት ወር ከተከሰተው ሁኔታ ጋር በማያያዝ የአውሮፓ እግርኳስ የበላይ ሀላፊዎች እና የብሪታኒያ መገናኛ ብዙሀን በፊፋ ላይ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ያለ-አግባብ ያወጁት የስም ማጥፋት ዘመቻ እንደሆነ በተደጋጋሚ ለመጠቆም የሞከሩ ሲሆን በተለይ ለብላተር ፕሬዝዳንት ሆኖ በተደጋጋሚ መመረጥ ሙሉ ድጋፉን በተደጋጋሚ የሰጠው የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን አባል ሀገሮች እና አብዛኛው ድምጻቸውን ለብላተር […]

Continue reading
Miruts Yifter 1

ማርሽ ቀያሪው

ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ ስፖርት በተለይ በረጅም ርቀት ሩጫ ውድድሮች አለማቀፋዊ ዝናን የተላበሱ እና የምንጊዜም ታላላቅ አትሌቶችን ለማፍራት የቻለች እና እያፈራችም ያለች ሀገር ስትሆን ከእነዚህ አትሌቶች መካከል “ማርሽ ቀያሪው” በሚለው ቅጽል ስሙ የሚታወቀው ምሩጽ ይፍጠር አንዱ ነው። ይህ ፖድካስት ስለታላቁ ኢትዮጵያዊ አትሌት ምሩጽ ይፍጠር ይዳስሳል። ዝግጅቱን እዚህ ያድምጡ።

Continue reading
Letesenbet - Gold

ኢትዮጵያ 41ኛው የአለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮናን በበላይነት አጠናቀቀች

በቻይናዋ ጉያንግ ከተማ አስተናጋጅነት ቅዳሜ (March 28, 2015) እለት በተካሄደው 41ኛው የአለም አገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በሜዳሊያ ሰንጠረዡ የበላይነትን ይዛ አጠናቀቀች። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በግል ለተሰንበት ግደይ በወጣት ሴቶች፣ ያሲን ሀጂ በወጣት ወንዶች ባገኟቸው የወርቅ ሜዳሊያዎች እንዲሁም በቡድን ባስመዘገቧቸው ሶስት የወርቅ ሜዳሊያዎች በመታገዝ በአጠቃላይ በአምስት ወርቅ፣ በሶስት ብር እና ሶስት ነሀስ ሜዳሊያዎች ሻምፒዮናውን በቁጥር […]

Continue reading
HELSINKI, FINLAND - AUGUST 13:  Tirunesh Dibaba of Ethiopia (2ndR) poses for a picture with her teammates after the women's 5000 metres final at the 10th IAAF World Athletics Championships on August 13, 2005 in Helsinki, Finland. Pavey finished last. Dibaba won gold, Meseret Defar of Ethiopia (2ndL) won silver, Ejegayehu Dibaba of Ethiopia (L) won bronze and Meselech Melkamu of Ethiopia finished fourth.  (Photo by Michael Steele/Getty Images)

ኢትዮጵያ – አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና አትሌቶች

  በአትሌቶች እና በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መካከል በተደጋጋሚ የሚፈጠሩ ቅራኔዎች አንዳንዶቹ መፍትሄ ተገኝቶላቸው ሲፈቱ ሌሎቹ ደግሞ የመወሰን ስልጣን ያለው አካል እሱ ያመነበትን ነገር ብቻ የመጨረሻ አማራጭ አድርጎ በመውሰድ የሌሎችን አስተያየቶች ከማስተናገድ ይልቅ በራሱ ሀሳብ መነሻነት ውሳኔዎችን እና እርምጃዎችን እየወሰደ ዛሬ ላይ ተደርሷል። ከፌዴሬሽኑ ጋር ችግር በተፈጠረ ቁጥር አትሌቶች የራሳቸው የሆነ በጋራ የሚንቀሳቀሱበት እና ለመብታቸው የሚቆም […]

Continue reading
Commentators

የስፖርታዊ ውድድሮች ውበት የሆኑ ድምጾች

ስፖርታዊ ውድድሮችን ለተመልካች እና ለአድማጭ ከሚያሳምሩት ነገሮች መካከል በጨዋዎች እና ውድድሮች ወቅት የሚፈጠሩ ክስተቶችን ከማስደገፊያ መረጃዎች ጋር በማዋሀድ የራሳቸውን ስሜት አካተው የሚያስተላልፉልን ኮሜንታተሮች ይጠቀሳሉ። እኔም ልክ እንደ አንድ የስፖርታዊ ውድድሮች ተመልካች እና አድማጭ ትዝታዎችን ጥለውብኝ ካለፉ ምርጦች መካከል ገንዘቤ ዲባባ ብሪታኒያ በርሚንግሀም ውስጥ የ2 ማይል የአለም ክብረወሰን የሰበረችበትን፣ የ19 አመቱ ታዳጊ ወጣት ሊዮኔል ሜሲ ከመረብ […]

Continue reading
Yidnekachew tessema

ዘረኝነትን እና ቅኝ ገዢዎችን የታገለው የአፍሪካ እግርኳስ

የአፍሪካ እግርኳስ የተለያዩ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እንቅፋቶችን አልፎ ዛሬ ያለበት ደረጃ ደርሷል። የአህጉሪቷን እግርኳስ የሚመራው የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን ካፍ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ ዘረኝነትን እና ሌሎች መሰናክሎችን ቢታገልም አሁንም ድረስ እንቅፋቶች በተለያየ መልኩ ከውስጥ እና ከውጪ እያጋጠሙት ነው። ለመሆኑ ይህ በተለያዩ እንቅፋቶች ውስጥ ያለፈው የአፍሪካ እግርኳስ እና የተለያዩ ችግሮችን እየተጋፈጠ ዛሬ ያለበት ደረጃ ላይ የደረሰው […]

Continue reading
Menotti 2

አጫሹ የእግርኳስ ሊቅ – ሜኖቲ

የአርጀንቲና እግርኳስ በውጤታማነቱና በሚያፈራቸው ኮከብ የእግርኳስ ተጨዋቾች ዛሬ ያገኘውን አለማቀፋዊ ዝና እንዲያገኝ ከፍተኛውን ሚና ከተጫወቱት ሰዎች መካከል አንዱ ሴዛር ሉዊስ ሜኖቲ ናቸው። የሜኖቲ ስም ሲነሳ አርጀንቲናዊያንም ሆኑ የተቀረው አለም የእግርኳስ አፍቃሪ አእምሮ ውስጥ ቀድሞ የሚመጣው ነገር ራሳቸውን ሜዳ ላይ በነጻነት መግለጽ በሚችሉ ተጨዋቾች የተገነባ ለአይን የሚማርክ እግርኳስ የሚጫወት ቡድን የሚል ነው። ሜኖቲ በእግርኳስ ተጨዋችነታቸው ሳይሆን […]

Continue reading
Follow

Get every new post delivered to your Inbox.